የሸዋንዳኝ የዘፈን ግጥሞች ከ ስጦታሽ

ስብርብር
ግጥም ቴዎድሮስ ካሣሁን
ዜማ ቴዎድሮስ ካሣሁን እና ሸዋንዳኝ ሃይሉ
ፈርቶ ራደ ልቤ ለስንት የገመትኩት
ወዶ እንደሚከዳኝ እኔስ መች አወኩት
ሊነግራት ሲከተል ፈራና ስሜቴ
ዛለ ዛለ ጉልበቴ  ዛለ ዛለ ጉልበቴ
ዛለ ዛለ ጉልበቴ  ዛለ ዛለ ጉልበቴ
ልብ ወዶ በፍቅር ሲበገር
ጉልበት እንደፋኖስ ቢሰበር
አይደምቅም በፍቅር ለዛለ
ሲወዱ ጀግንነት የታለ
ልብም ካልረገጠ ሆኖ አቻ
እግር አይራመድም ለብቻ
መሄዱን ወደሷስ እሄዳለሁ
ግን አላውቅም የትጋ እንዳለሁ
ድክምክም አለብኝ ዛለና ጉልበቴ
ሰጋ ሰውነቴ
ስብርብር አለብኝ ጉልበቴ
እሷን ሲያይ የት ሄደ ድፍረቴ
ለመውደድ እንዳይሆን ሆኛለሁ
ኣ አቃተኝ ኧረ እኔስ ዝያለሁ
ስብርብር አለብኝ ጉልበቴ
እሷን ሲያይ የት ሄደ ድፍረቴ
ለመውደድ እንዳይሆን ሆኛለሁ
ኣ   አቃተኝ ኧረ እኔስ ዝያለሁ
ስብርብር አለብኝ ጉልበቴ
እሷን ሲያይ የት ሄደ ድፍረቴ
ለመውደድ እንዳይሆን ሆኛለሁ
ፈርቶ ራደ ልቤ ለስንት የገመትኩት
ወዶ እንደሚከዳኝ እኔስ መች አወኩት
ሊነግራት ሲከተል ፈራና ስሜቴ
ዛለ ዛለ ጉልበቴ  ዛለ ዛለ ጉልበቴ
ዛለ ዛለ ጉልበቴ  ዛለ ዛለ ጉልበቴ
ሲመሽ ባልጋ ላይ ተኝቼ
በሀሳቤ በራፍ ወጥቼ
ከሷ ጋር ለማደር እሄዳለሁ
ቀንማ ፈርቻት እቀራለሁ
ልብ ወዶ በፍቅር ሲበገር
ጉልበት እንደፋኖስ ቢሰበር
አይደምቅም በፍቅር ለዛለ
ሲወዱ ጀግንነት የታለ
ድክምክም አለብኝ ዛለና ጉልበቴ
ሰጋ ሰውነቴ
ስብርብር አለብኝ ጉልበቴ
እሷን ሲያይ የት ሄደ ድፍረቴ
በመውደድ እንዳይሆን ሆኛለሁ
ኣ አቃተኝ ኧረ እኔስ ዝያለሁ
ስብርብር ስብርብር
ዛለ
አለብኝ ጉልበቴ




ስትስቂ ሳይ
ዜማ ጌትሽ ማሞ
ግጥም ይልማ ገ/አብ እና  ጌትሽ ማሞ
ስትስቂ ሳይሽ በውብ ፈገግታሽ
የልቤ አሳብ ጭንቀቱም ይለቀኛል
ፊትሽ በሳቅ ሲፈካ ደስ ይለኛል
ስትስቂ ሳይ ደስታሽን ሳይ
ደስ ይለኛል ካንቺ በላይ
ሳምንት ሆነ ብደክም ወይ አመታት
ይመለሳል ብንቺ ሳቅ የኔ ብርታት
ያምርብሻል ሁልጊዜም ተጫወቺ
አንቺ እንደሆንሽ ለፀብም አትመቺ
ሳ--- ሳቂልኝ     ሳ--- ሳቂልኝ    ሳ--- ሳቂልኝ
ሳቂልኝ    ሳቂልኝ    ሳቂልኝ    ሳቂልኝ    ሳቂልኝ    ሳቂልኝ
መሽቶ ነጋ ምንጊዜም የትም ቦታ
ካፍሽ በራፍ ይዘንባል ሳቅ ጨዋታ
ነፍሴ እድሜዋን ቀጠለች ባንቺ ረክታ
የዐይኖችሺን ወጋገን ተመልክታ
ሳ--- ሳቂልኝ     ሳ--- ሳቂልኝ     ሳ--- ሳቂልኝ   
ሳቂልኝ    ሳቂልኝ    ሳቂልኝ    ሳቂልኝ    ሳቂልኝ    ሳቂልኝ   
ስትስቂ  ሳይ ደስታሽን ሳይ
ደስ ይለኛል ካንቺ በላይ




ስሜስ
ግጥምና ዜማ ቴዎድሮስ ካሣሁን
ስሜስ የማን ነው ልኔ አብሮኝ ከሌለ
አንቺን ሲጠሩሽ አፌ አቤት እያለ
እኔ እንደዚህ እስኪሳነኝ አቅም
ሰው ወድጄ አላውቅም
ካንዴም ሁለቴ ልቤ ቢያግም ወዶ
መች አፈቀረ ይህን ያህል ሄዶ
እንዴት አድርጌ ብወድሽ
አቤት ልበል በስምሽ
ከፍቅር ባህር ብጠልቅም
እንዲህ ወድጄ አላውቅም
ስሜስ የማን ነው ልኔ አብሮኝ ከሌለ
አንቺን ሲጠሩሽ አፌ አቤት እያለ
እኔ እንደዚህ እስኪሳነኝ አቅም
ሰው ወድጄ አላውቅም
በመልክሽ ፀሀይ ሲነጋ ሌሊቴ
ድምፅሽ አነቃኝ ከብቸኝነቴ
ሆነሽ የፍቅር ዘማሪ አቤት እንደወፍ ስታምሪ
አይኔ ሲከተል ልብሽን
ተግልጦ አየሁት ልብሽን
በመልክሽ ፀሀይ ሲነጋ ሌሊቴ
ድምፅሽ አነቃኝ ከብቸኝነቴ
ሆነሽ የፍቅር ዘማሪ አቤት እንደወፍ ስታምሪ
አይኔ ሲከተል ልብሽን
ተግልጦ አየሁት ልብሽን
የመልክሽ ጀንበር ጨለማውን ጥሶ
ድምፅሽ አነቃኝ ማለዳ ገስግሶ
ሆነሽ የፍቅር ዘማሪ አቤት እንደወፍ ስታምሪ
አይኔ ሲከተል ልብሽን
ተግልጦ አየሁት ልብሽን
ባሳብ አብሬሽ በራለሁ
ሶረኔ ሲሉሽ ዞራለሁ
ሆነሽ የፍቅር ዘማሪ አቤት እንደወፍ ስታምሪ
አይኔ ሲከተል ልብሽን
ተግልጦ አየሁት ልብሽን
ባሳብ አብሬሽ በራለሁ
ሶረኔ ሲሉሽ ዞራለሁ







ስጦታሽ
ግጥም ይልማ ገ/አብ  ዜማ  ጌትሽ ማሞ
መውደድ ነው የማነብብሽ
ፍቅር ነው የማይብሽ
በማንም ሳትለውጪኝ
ራስሽን የምትሰጪኝ
አይታይ ውለታሽ ያረግሺው አብረን በኖርነው
ስጦታሽ የማይጠፋ ፍቅር ነው
የመውደድ ራቤን ማሰብሽ ሲሞላው
ጉርሻሽ አይታየኝ በእጅሽ የምበላው
የታወቀ ግዜ ሁኔታሽ በአንድ ላይ
እንዳይሆን ያስፈራል ፍቅርሽ ካቅሜ በላይ
ኧረ ምነው ባይበዛብኝ ምነው
ኧረ ምነው ውለታሽ ብዙ ነው
 መውደድ ነው የማነብብሽ
ፍቅር ነው የማይብሽ
በማንም ሳትለውጪኝ
ራስሽን የምትሰጪኝ
አይታይ ውለታሽ ያረግሺው አብረን በኖርነው
ስጦታሽ የማይጠፋ ፍቅር ነው
ስጦታሽ ሁልጊዜ ሳይወጣ ተግልጦ
ተሸፍኖ ያምራል ከሚታየው በልጦ
የታመናል እንጂ እውነት መች ይካዳል
ስለማይወራ  ውለታሽ ይከብዳል
ኧረ ምነው ባይበዛብኝ ምነው

ኧረ ምነው ውለታሽ ብዙ ነው

No comments:

Post a Comment