ግጥሞች
ለመልቲዎች
የሰው
መልቲ የሰው ብልጡ
ልፋት
ጠሩ ሥራ ምጡ
አንደኛው
ላይ ተንጠላጥሎ
አንዱን
ገፍቶ አንዱን ገሎ
ብድግ
ብድግ ቶሎ ቶሎ
ልብ
ሳይርድ
ሳይገመስ
አንጀት
ሳይነድ
ሳይላወስ
ዓይን
ሳይፈዝ
ደክሞ
ሳይቀዝ፣
እግር
ሳይቀጥን
ሳይሰለስል
ላቦት
ሳይተን
ጠብ
ሳይል
ቆሽት
ሳይበግን
ሳይቃጠል፣
ጉልበት
ሳይልም
አልቆ
ሳይዝል
አንጎል
ሳይደክም
ህዋስ
ሳይገል፣.
በሰው
ጉልበት በሰው ጫንቃ
በአንዱ
ልፋት ባንዱ ሲቃ
እሱነቱ
ሰውነቱ
ጸጉር
ጥፍሩ ህዋሳቱ
በወከባ
በግርግር
በሽው
ሽው በውዥንብር
ተገምብቶ
በሰንበሌጥ
ተወሻሽሎ
በልጣልጥ
ተገምድሎ
ተቦትቶ
በድኑ
እንጂ ሩሑ ጠፍቶ
በክረምቱ
ሰኔ ታርሶ
ተሸፋፍኖ
አፈር ለብሶ
ከምን
ግዜው ተመልሶ
አረም
ሆኖ ዳዋ ለብሶ
ግራ
ቀኙ ተቀላቅሎ
እላይ
ታቹ ተመሳቅሎ
ሲዘቀዝቅ
ሲያዘነብል
ታች
ታች ሲለው ሊከነበል፣
የዛን
ጊዜ አወይ ጉዱ
ምን
ይል ልቡ ምን ይል ሆዱ
በቀረበት
እኩይ ልምዱ
ወይ
መኖሩ መወለዱ::
በላቸው ገላሁን፣ ጥቅምት ፳፻፫
መንፈስ ዘመብረቅ
ደመና
ባዘለው፣ ጉም ባፈነው ሰማይ
እኛ
. . . ታች! . .
. አንተ . . . ላይ!
ከካፊያው
ነጠብጣብ ልንሸሽ ስንሯሯጥ
ስንሮጥ
ስንራወጥ፣
ስንወድቅ
ስንነሳ፣ ስንቆጥር አበሳ፣
ፍዳችንን
ስናይ . . .
ለገነት
መሳቂያ፣
ሕይወት
ማዳመቂያ፣
እንድንሆን
ብለህ፤
በአምሳለ
መብረቅ፣
ፎቶ
እንዳነሳኸን . . .
ዛሬም
በአሩሩ፣
በብርድ
በቁሩ፣
በረኀብ
ስንቆላ፤
ፍቅር
ጠፍቶ፣ - ቢላ፣
ተቀባብለን
ባላ፣
እርስ
በርስ ተጋድለን፣
አምሳልህን
‘ረስቶ፣
ሰው
ለሠራው ሞቶ፤
ምድራችን
ገልምታ፤
በሰው
ሥጋ ሸትታ፤
ደምም
ሆኖ ጤዛ፣
ምድርን
ሲያወረዛ፣
አፈርን
ሲያወዛ፣
በምስቅልቅል
ኑሮ፣
ካ‘ንዱ ቤት ከበሮ፣
ካ‘ንዱ ቤት እሮሮ፣
ሲሰማ
ሲወራ፣
የችጋር
መከራ፣
ሲረገጥ
ዳንኪራ፤
ዛሬም
አንተው ቀርበህ፣
ደመናውን
ገልጠህ፣
ሰማዩን
ሰንጥቀህ፣
ገጭ
አድርገን ፎቶ፤
‹‹እግዚኦ››
እንዲባልልን
በቅዱሳን
ታይቶ::
ዮሐንስ ሞላ ‹‹የብርሃን ልክፍት›› (2005)
እጦት ለፋፊዎች
ከሳምባ ነቀርሳ
በነፃ
ኤክስሬይ ስንነሳ
ዕርቃናችንን ነበርን
አንድ ሃያ ሰዎች፡-ባንራብም
የጠገብን እማንመስል፣
ብንጠግብም
የተረፈን እማንመስል
የጦት ዘመን ሰዎች
እጦት ለፋፊዎች፡-ልብሳችን ጨርቅ
የመርፌ ጥቅጥቅ፤
እግራችን ባዶ
ንቅ
የጭቃ ጭምልቅ፤
ጎድናችን የሚቆጠር
አጥንተ ውትርትር
የማነን?
የኔ የሚል ጎበዝ
እስቲ ብቅ
አለበት ብዙ መዘዝ::
ሰይፉ መታፈሪያ
ፍሬው ‹‹የተስፋ እግር ብረት››
ደራሲ
ማን ነው?
አንተ ባለቅኔ! አንተ ልብ-ወለድ
ወላጅ
ሥነጽሑፍን ከሕዝብ ገንጥሎ ተራማጅ::
ከመካከል ቁመህ ደረትህን አትንፋ
ወይ እሳቱን አንድድ ወይ እሳቱን
አጥፋ…
ወይ ነፋሱን አግድ ወይ ነፋሱን
ግፋ
ወይ ደመናን ጥረግ ወይ ደመናን
አስፋ
ወይ ትንፋሽህን ዋጥ ወይም ትንፋሽ
ትፋ::
ወይ ዐይንህን ግለጥ ወይ ዐይንህን
ዝጋ
ወይ ጀሮህን ድፈን ወይ ጀሮህን
አትጋ::
ወይ ታጠቅ ተፈሪ ወይም ታጠቅ ቁምጣ
ወይም ፀሐይ አግባ ወይም ፀሐይ
አውጣ::
አልሚ-አጥፊ ተብለህ አብጅ ዘመድ
ጓድ
ሁለት የወደደ አያገኝም አንድ::
ነፋስ አንከባሎም ወደ አንዱ አይጎልትህ
መጥፎና መልካሙን ሳይመርጥ
ጭንቅላትህ::
ሥነጽሑፍ የሕዝብ ናት የሰፊው ሕዝብ
ምርጫ
የላትም ጉራንጉር የግል መሸጎጫ
የልፍኝ ቤት መግቢያ… የጓሮ በር
መውጫ::
እና! የምንለው የደራሲው ብዕሩ
ወይም ከሕዝብ ሆኖ ቀይ ይሁን
መስመሩ::
ከሕዝቡ ደም ነክሮ ይጻፍ የሕዝብ
ዋይታ
ወይም ከውሃው ጠቅሶ በውሃው ግጥም
ይምታ::
ከሁለቱ መርጦ ባንደኛው ካልጣፈ
ለደሙም ለውሃውም ጠላት ነው የጦፈ::
ግን ከመኸል ቁሞ መንገዱን ከዘጋ
ኸንጥ ይግባ ተገፍቶ ምን አለው
ከእኛ
አያልነህ ሙላቱ ‹‹ወይ አንቺ አገር›› (2004)
ሕይወት ቅኔ
ሕይወት ማለቅ ቅኔ
ለእኔ ማለት የእኔ::
ወይም ሕይወት ሞፎ
የእኔነት ቀፎ::
በራሴ ውስጥ ያለ ያገር ፍቅር ወኔ
ባህል ኪነ ጥበብ ማህሌተ ቅኔ::
በመብላት … በማግሳት … ሕይወት
ከታመነ
ጓዱ በዓለም የለም አካሉ ካልሆነ::
ካለዚያም መቀመጥ … መወዘፍ በሶፋ
ከሆነ የሕይወት እሷነት ይጥፋ::
ወይም እኔነቴ በእኔ ዘንድ አይኖርም
ወደ ኋላ አይሔድም … ወይ ወደላይ
አይበርም
እሱም … እኔም … ግጥሜም ..
እንድንቆይ ባንድ ዕድሜ
እኔ ግጥም ልጻፍ … ታግሎ ይኑር
ግጥሜ
ካሊያ ግን አልገፋም ኑሮን በዝም
ትርጉም
ኑሮ እራሷ ትሁን የረከበች እርጉም
ሕይወት ከነምኗ . . .
ትበል እልም … ድርግም
አያልነህ ሙላቱ ‹‹ከድጡ ወደ ማጡ! የግዛተ
-
ደርግ ግጥሞቼ ፲፱፻፷፰-፹፪›› (2004)
እናጨበጭባለን!
ግዴለም
ስግደቱን፣
ሺ ጊዜ እንሰግዳለን
ሺ ዓመት ንገሡ
ምስጋና አንነፍግም፣
ክብር አናጎድልም፣
በጣም ተወደሱ፡፡
ማዕረግ፣
ደረጃውን፣
ቅጥያ አንገድፍም
ስም አንገረድፍም
ሠርተዋል!
ለፍተዋል!
ደክመዋል! ጥረዋል
ብለን በጭብጨባ
ሹመቱን፣
ዝናውን
ሥልጣኑን መርቀን
ስም እናፀድቃለን
ምስጋና እንሰዋለን፡፡
እንዲህ
በጭብጨባ
ሙቀው አሟሙቀው
እጆች ካልተኮሱ
ገንዘብ
ወርቃችንን
ዘርፋችሁ ስታፍሱ
ያለቁጭት
ችለው
ዱላም አያነሡ፡፡
ውዳሴ ፈረደ
ተገኘ ‹‹በራማ ሸለቆ›› (2004)
ፈሪ ቁም
“ፈሪቁም - ፈሪቁም፣
ምንተ ላል-ይበላ
ሲሸሽ የሞተሰው፣
ተዝካሩ አይበላ::”
እንዲል ያበው ብሂል
ሁሉም የየራሱን፣ የመከራ መስቀል
ደፍሮ በመሸከም፣ ሳይደማ-ሳይቆስል
ሞት ሳይኖር፡ ትንሣኤ፡ የሚገኝ ይመስል…
ስንቶች እዚያ ማዶ፡ ከነጭ ሠራሹ
የነገደ ያንኪን
መንግሥተ-ሰማያት፣ ለመውረስ የሚሹ
(ያውም በቀውጢ ቀን)፡
ያቺን ምስኪን አገር፡ እየጣሏት ሸሹ::
ሰሎሞን ሺፈራው
“ተወራራሽ ሕልሞች”
(2004)
No comments:
Post a Comment