ሄዋን እንደዋዛ
ልቤም ተደላደለ ጎኔም ደላው መሰለኝ
አንችን ስለመውደዴ አገር ሰምቶ ጉድ ቢለኝ
ከወደድኩሽ ወዲያ ምንድንነው ቢጠፋም ስሜ ነው
በዚች አለም ስኖር-----ሰው ነበር ረሀቤ
ምኞቴ ተሳካ----ባንቺ አረፈ ልቤ
ወሬ ቢጓዝ በቀን---በሌሊት ጨረቃ
አንች አለሽኝ ለኔ----ስም አልፈራም በቃ
ካበጀሽ ፈጣሪ----ከኔ ወስዶ ለኔ
እንዴት እኖራለሁ----ያለግራ ጎኔ
ሄዋን እንደዋዛ----ፍሬዋን በልተሽ
በኔና በምድር--ሞት እንዳመጣሽ
ለባከነው ልቤ----ራርቶ ልብሽ
መጽናኛ ሆኖኛል----ክሶኛል ፍቅርሽ
ፍቅራችን ይወሰን----ይሁን አቻ ለአቻ
እኔም አንችን ብየ------አንችም እኔን ብቻ
ተረታና ልኔ ለፍቅር----- ለፍቅር ተገዛ
በሆዴ ቤት ሰራች-----ሄዋን እንደዋዛ
ሄ------ዋን እንደዋዛ
ሄ------ዋን እንደዋዛ
እንደዋዛ
ሄ------ዋን እንደዋዛ
እንደዋዛ
ልቤም ተደላለ ጎኔም ደላው መሰለኝ
አንችን ስለመውደዴ አገር ሰምቶ ጉድ ቢለኝ
ከወደድኩሽ ወዲያ ምንድንነው ቢጠፋም ስሜ ነው
ሲባክን አንጀቴ-----የሀሳብ ስንቅ ይዞ
አበቃልኝ ዛሬ------ የብቻየ ጉዞ
ልቤ ባንች ነቅቶ ከተደላደለ
ስሜ ቢዞር ባገር----ቢጠፋስ ምን አለ
ካበጀሽ ፈጣር------ከኔ ወስዶ ለኔ
እንዴት እኖራለሁ---ያለግራ ጎኔ
ሄዋን እንደዋዛ ፍሬዋን በልተሽ
በኔና ለምድር ሞት እንዳመጣሽ
ለባከነው ልቤ ራርቶ ልብሽ
መጽናኛ ሆኖኛል ክሶኛል ፍቅርሽ
ፍቅራችን ይወሰን ይሁን አቻለአቻ
እኔም አንችን ብየ አንችም እኔን ብቻ
ተረታና ልኔ በፍቅር ተገዛ
በሆዴ ቤት ሰራሽ___ሄዋን እንደዋዛ
ሄ------ዋን እንደዋዛ
ሄ------ዋን እንደዋዛ
እንደዋዛ
ሄ------ዋን እንደዋዛ
ልቤ መጨነቁን
ልቤ መሸነፉን-----እንዳይነግራት ሰጋ
ወራትም አለፉ------ክረምትና በጋ
የሆዴ መጨነቅ-----ፍቅሬ መች ገባት
ትስቃለች እሷ-----ልጅነት ይዟት
በውበት ቁንጅና-----መልኳ መች አነሰ
ቀርቤ እንዳልነግራት----ልጅነቷ ባሰ
የሆዴ መጨነቅ----ባይገባት ነው ለእሷ
ቀርቤ ስነግራት------የሚስቀው ጥርሷ
ልቤ መሸነፉን------እንዳይነግራት ሰጋ
ወራትም አለፉ----ክረምትና በጋ
ተይ አስታሚው------መራቅሽን
ግፍ አትስሪ----ጡር አለው ፍቅር
እንዴት ልርሳሽ----ከሆዴ አውጥቼ
ባይንሽ ውበት-----እዳ ገብቼ(3)
አስረሽኛል አልላወስም-----እስቲ ፍቺኝ በይ እንደ ቄስ
እንዳልከስሽ ለመሪጌታ-----ከልጅ ውሎ [የለም ስሞታ](3)
ልቤ መሸነፉን-------እንዳይነግራት ሰጋ
ወራትም አለፉ--------ክረምትና በጋ
የሆዴ መጨነቅ-----ፍቅሬ መች ገባት
ትስቃለች እሷ-----ልጅነት ይዟት
ልነግራት እልና-----ነገ ዛሬ እያልኩ
የፍቅርን ረመጥ-----አዝየው ከረምኩ
ሆዴ ላይሆንለት-----እንዲያው ተጨነቀ
ሁኔታዋ ሁሉ----ነፍስ እንዳላወቀ
ልቤ መሸነፉን-----እንዳይነግራት ሰጋ
ወራትም አለፉ------ክረምትና በጋ
የሆዴ መጨነቅ-----ፍቅሬ መች ገባት
ትስቃለች እሷ-----ልጅነት ይዟት
አሳምሮ ወበት ቢያድላት ፍቅር አታውቅም ልጅነት አላት
ተመኝቸው ድንቅ ውበቷን እንዴት ላድርገው [ልጅነቷን](3)
ቀድማ ስቃ ቀልቤን ገዛችው
ልቤን ማርካ ደጅ አስጠናችው
ወይ አጸድቅብኝ አዝና ለነፍሷ
ትስቃለች ተይዤ በሷ ተይዤ ነሷ
አሳምሮ ውበት ቢያድላት ፍቅር አታውቅም ልጅነት አላት(2)
ተመኝቸው ድንቅ ውበቷን እንዴት ላድርገው [ልጅነቷን](2)
No comments:
Post a Comment