በዛብህ
እናትና
አባቴ በስለት ወልደውኝ
ለስለታቸው
መልስ ለካህኑ ሰጡኝ
የሰጣቸው
ጌታ ከቅይሩ ሊያኖረኝ
ባካባቢው
ካህናት ቅኔን አስተማረኝ
አሐዱ
አምላክ ብዬ ዳዊቴን ደግሜ
ሰዓታት
ወረቡን ቅዳሴውን ቆሜ
በለጋው
ዕድሜዬ ጥበብን ተክኜ
ላፈሩኝ
ወላጆች ከልብ ለተሳሉት
ላያዩኝ
ላይድሩኝ መልሰው ለሰጡት
ለነሱ
አልሆን ብዬ ከሱ ተጠግቼ
እንደ
ጧፍ በራሁኝ ታየሁኝ ጎልቼ
የኔ
ጎልቶ መውጣት ስለቱን ፈተነው
የውስጤን
ሊለካ አየኝ ፊት አውራሪው
ከጌታው
መኖሪያ ከባለፀጋው ቤት
አለች
እፀ በለስ ነብሴ የምትሰጋት
ውበትዋ…
ያማረ ሰብል ነው እኔ የማልነካው
ባለፍኩበት
ቁጥር ውስጤን ከስር የሚያናጋው
ፊደል
ባስቆጠርኩኝ እንዳባቷ ት’ዛዝ
ታዝብኝ
ጀመረች የፍቅርን ትኩሳት
እኔ
የስለት ልጅ እሷ እፀ በለስ
ድሮ
ተዘግቶብኝ ሁሉ ማይቀመስ
የአጥሩ
መብዛት ከዘሮቿ ደጅ
ምንም
ብንካጀል የለን አማላጅ
የሁለታችንም
ልብ ነጎደ ሌላ ‘ለም
እያወቅነው
የስለቱን የጌታውን ሕመም
ለሕዝብ
አልተመቸ ለፈጠረኝ ጌታ
ከቀዬ
ሲያባረኝ የስለት ከርታታ
ዲማ
ጊዮርጊስም እንቢ አለ ይኼንን መዋጋት
የ‘ፀ በለስ ጌታ የድሃ ሰው ስለት ክልክል የነገስታት
ፍቅሬ
ቢጠና አገር አቆራርጦ
አፈናቅሎ
ጣላት እሷን አስቆጥቶ
ገደልን
ፈንቅለን ተርበን ተጠምተን
ስለትን
እረግመን ሸሸን ነገሥታቱን
መቃብር
ሊወርደው ፍቅረ መውደዳችን
ባላሰብነው
መንገድ ባልጠፋበት ጊዜ
የፈጠረን
ጌታ ለፍቅር ለሐዘን ኑዛዜ
ሰጠን
ያችን ዕለት የመቃብር ፍቅር
ይዘነው
እንድንሄድ ሁሉንም በክብር::
ሔለን ካሳ “ግጥም እና እኔ” (2005)
No comments:
Post a Comment