ብሂሎች
“ሌላ መንገድ በመፈለግ ጊዜህን አታጥፋ መንገድ በፊትህ ነው:: ተነስቶ መራመድ ያንተ ፋንታ
ነው::
ቅ/አውግሰጢኖስ
“ልብህን ብሩህ አድርገው ዓለምን የምትመለከትበት መስኮት ነውና::”
ጆርጅ በርናርድ ሾው
“ሕይወት ራሷን ላለመጣል ከምትቀይሳቸው አቅጣጫዎች በአንዱ ውስጥ ማለፍ የግድ ነው::”
“ጥሩ ወይም መጥፎ የሚባል ነገር የለም፣ አስተሳሰባችን የሚፈጥረው እንጂ::”
ዊልያም ሺክስፒር
“ለሌሎች ካላሰብንና የምንችለውን ካላደረግንላቸው ከደስታ ምንጮች አንዱን እንዳደረቅን
እንገንዘብ::” ሬይ ሊመን ዊልበት
“ብዙ ሰዎች የሚደሰቱት ራሳቸውን ለደስተኝነት ባዘጋጁት መጠን ነው::”
አብርሃም ሊንከን
“መፍራት ያለብን ራሱን ፍራቻን ብቻ ነው::”
ፍራንክሊን ሩዝቬልት
“ጨለማን ሲረግሙ ከመኖር አንዲት ቁራጭ ሻማ መለኮሱ ይበጃል::”
ራልፍ ዋልደ ኢመርሰን
“ፍርሃትህን ለራስህ በጉያህ ሸሽግ ወኔህን ግን ከሌሎች ጋር ተካፈል::”
ሮበርት ሉዊስ ስቲቭንሰን
“ለራሱ በቂ ነገር እያለው በጋራ መጠቀምን የማይሻና በማኅበር ለመኖር እራሱን የማያስገድድ ሰው
ቢኖር ሰው ሳይሆን አውሬ መሆን አለበት::”
አርስቶትል
“ዛሬ ቀን ከሚገጥምህ ነገር ጋር ራስህን ለማስማማት ታገል እንጂ እኔ እንደፈለግሁት ካልሆነ
አትበል::”
አብርሃም ሊንከን
“አንድን ነገር በማወቅና በመረዳት መካከል ትልቅ ልዩነት አለ::”
ቻርለስ ካታሪንግ
ወርቃማው ህግ
ክርስትና
እንግዲህ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን
ሁሉ እናንተም ደግሞ እንዲሁ
አድርጉላቸው ሕግም ነቢያትም ይህ
ነውና:: (ማቴ 7÷12)
እስልምና
ለራሳችሁ የምትመኙትን ለሌሎችም
እንዲሆን እስካልተመኛችሁ ድረስ በትክክል
አላመናችሁም:: (የነብዩ መሐመድ
ተግባራትና ንግግሮች)
የአይሁዶች እምነት
አንተ የምትጠላውን ነገር በባልጀራህ
ላይ አታድርግ ይህ ነው እግዚአብሔር
ለሙሴ የሰጠው ሕግ ሲጠቃለል::
(ሒላል ታልሙድ ሻባት 31)
የባሃኢ እምነት
በአንተ ላይ ሊጫንብህ የማትፈልገውን
በሌላ ላይ አታድርግ በራስህም ላይ
እንዲደርስብህ የማትሻውን ለማንም
አትመኝ:: (ባሀኡላህ)
ቡዲሂዝም
ራስህን የሚጎዳ የሚመስልህን ነገር በሌሎች ላይ አታድርግ::
ሒንዱዝም
አንተ ላይ ቢደረግ የሚያስከፋህ
ከሆነ አንተም በሌሎች አታድርግ የተግባር ሁሉ
ማጠቃለያ ይህ ነውና:: (ማኅበራታ
51517)
ጃኒዝም
ማንም ሰው ለራሱ እንዲደረግለት
የሚሻውን እርሱም እንዲሁም በዓለም ዙሪያ
ላሉ ፍጡራን ሁሉ ያድርግ:: (ማሃቪራ
ሱትራክሪታንጋ)
ሲኪሂዝም
ለማንም ባይተዋር አይደለሁም ማንም
ለእኔ ባይተዋር አይደለም የሁሉም ወዳጅ
ነኝ:: (ጉሩ ግራንትዝ ሳሂብ ፒጂ.1299)
ዩኒታሪያኒዝም
ሁላችንም አካል የሆነበትን የፍጥረታት
አንድነትና ትስስር በጽኑ እንደግፋለን
እንዲሁም ልዩ አክብሮት እንዲሰጠው
እንተጋለን:: (የዩኒታሪያን መርሆ)
ታኦዝም
ጎረቤትህ ሲያተርፍ አንተ እንዳገኘህ
ቁጠር ጎረቤትህ ሲከስር አንተ እንዳጣህ
አድርገህ ውሰድ:: (ቲአይ ሻንካ
ካንዩንግ ፒዮን 213-218)
ኮንፉሺያኒዝም
የመልካም ሥነ ምግባር መሠረት ማጠቃለያ
የሆነ አንድ ቃል ነው እሱም
ሩህሩህ መሆን በአንተ ላይ ሊደረግ
የማትፈልገውን በለሎች ላይ አታድርግ::
(ኮንፍሺየስ አናሌክትስ 15.23)
ዞሮአስትሬይኒዝም
አንተን የሚጎዳ ነገር ሁሉ በሌሎች
ላይ አታድርግ:: (ሻያስት-ና-ሻያስት 13.29)
ኔቲቭ ስፒሪቹአሊቲ
የኛ ሕልውና የሚረጋገጠው የምድራችን
ተፈጥሮ ይዞታ ሲጠበቅ ነው:: (ቺፍ ዳን ጆርጅ)
ኢንተርፌዝ ፒስ ቢዩልዲንግ ኢንሽየቲቭ
No comments:
Post a Comment